ወቅታዊ የሀገራችን የኮንስትራክሽን ሁኔታ

ወቅታዊ የሀገራችን የኮንስትራክሽን ሁኔታ

                  ሀገራችን በአሁኑ ሰዓት ከሌላው ጊዜ በበለጠ ለኮንስትራክሽን ዘርፍ ትኩረት የሰጠች ቢሆንም ብዙ የኮንስትራክሽን ዘርፍ ተቋማት አሁን ባለው የግንባታ እቃ የዋጋ ንረት ምክንያት ስራቸውን እንደፈለጉት ባሰቡት ልክ ለማሳካት ማነቆ ሆኖባቸዋል ፣ አብዛኞቹ ተቋማት ስራቸውን በጊዜያዊነት እና በቋሚነት ለማቆም ተገደዋል ፡፡

     ለዚህም  ምክንያቱ የሀገራችን አብዛኛው ግንባታ የሚካሄደው ኋላቀር በሆነ ቴክኖሎጂ መሆኑ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ጊዜያችን በአግባቡ ሳንጠቀም የግንባታ እቃ መዋዠቅ እና የጊዜ ኪሳራ ውስጥ እንገባለን፡፡ለነገሩ በአሁኑ ሰዓት ኮንስትራክሽን ላይ ብቻ ሳይሆን እያንዳንዱ ለአገልግሎት የሚውል ጥሬ እቃ ፣ ለምግብ ፍጆታ የሚውሉ እና ሌሎችም  በዓለም ዐቀፍ ደረጃ ነው የዋጋ ንረቱ የተከሰተው፡፡

              ድርጅታችን ሐምብራ ቢዝነስ ግሩፕ አ.ማ በኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂ በኩል የራሱ አስተዋጠፆ ለማድረግ እና ኮንስትራክሽኑን ለማዘመን እቅድ እና ግብ ይዞ ተነስቷል፡፡ የተሻለ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመጠቀም እቅዱን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማሳካት ቆርጦ ተነስቷል፡፡


እስካሁን ድረስ አስተያየቶች የሉም